ቀይ ስጋ ለጤና አስጊ ሆነ

Your browser doesn’t support HTML5

አሜሪካዊያን በአማካይ አብዝተው ስጋ ይመገባሉ። እንደ ዶሮና ተርኪ ካሉ ነጭ ስጋዎች በይበልጥ ቀይ የከብት ስጋ ላይም ያተኩራሉ። እንደሚታወቀው ስጋ ደግሞ በፕሮቲን የተሞላ ነው። ረጅምና ጤናማ ህይወት ለመምራት የስጋ አመጋገብን መቀነስ፣ አትክልቶች አብዝቶ በመመገብ ለሰውነት የሚያስፈልገውን በቂ ፕሮቲን ለማግኘት ይቻላል ይላል አዲሱ ጥናት።