ጦርነቱ የሥራ ዕድል ፈጠራን አስተጓጉሏል

Your browser doesn’t support HTML5

ዓመታዊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዕቅዱን ማሳካት እንዳልቻለ የኢትዮጵያ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ከሚል ዛሬ በሰጡት መግለጫ ጦርነቱ በቴክኒክና በሙያ ተቋማት ላይ አሥር ቢሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት እንዳደረሰ አመልክተዋል።

የትምህርት ተቋማትና ማሠልጠኛ ማዕከላት የሚሰጧቸው ሥልጠናዎች ገበያ ተኮር አለመሆን ለሥራ አጥነት አስተዋፅዖ ማድረጉን ጥናታዊ ፅሑፍ ያቀረቡ አንድ ምሁር ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የአሠሪዎች ፌዴሬሽን ደግሞ ባለሙያ ማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጿል።