የኢትዮጵያ ኅገ መንግሥት ስለ ጋዜጠኝነት ምን ይላል? ሌሎች ተዛማች ኅጎችስ?

የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃንና እነርሱን የሚገዙት ልዩ ልዩ የአገሪቱ ኅጎች ሁነኛ የኅግ ማሻሻያዎችና የፖሊሲ ለውጦችን ከሚሹ አበይት ጉዳዮች ውስጥ ናቸው፤ ሲሉ የተለያዩ ወገኖች እየተናገሩ ነው።

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ኅጎችና የመገናኛ ብዙኃን፤ ትንታኔ የመጀመሪያ ክፍል



Your browser doesn’t support HTML5

ትንታኔ፥ ክፍል ሁለት


የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አጀማመር፥ የዛሬ ይዞታና መጪ ሁኔታ በተከታታይ ውይይቶች የምንመለከታቸው ጭብጦች ናቸው።

የኢትዮጵያ ኅገ መንግስት ስለ ጋዜጠኝነት ምን ይላል? የጸረ ሽብር ኅጉ አንድምታ?

በዚህ ባለ ሁለት ክፍል ቀዳሚ ውይይት፥ የመሠረታዊን የሰው ልጆች የንግግር ነጻነት ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ጨምሮ የአገሪቱን ኅጎች ትርጓሜና ምንነት እንመረምራለን።

ከአንጋፋና ከወጣት ጋዜጠኞች፥ እንዲሁም ከፈቃድ ሰጪና ተቆጣጣሪው የመንግስት መሥሪያ ቤት ባለ ሥልጣናት ጋር በተከታታይ የሚካሄዱ ቀጣይ ውይይቶች በአንጻሩ የወቅቱን የአገሪቱን የብዙኃን መገናኛዎች ይዞታና መጪውን አቅጣጫ ለማመላከት ይጥራሉ።