የህወሓት ከፍተኛ የአመራር አባላት ተደመሰሱ ሲል መንግሥት አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ ከፍተኛ የአመራር አባላት የነበሩትን “ስዩም መስፍንንና አባይ ፀሐዬን ጨምሮ አራት ሰዎች ተገድለዋል” ሲሉ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስቴር የኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብሪጋዲየር ጄነራል ተስፋዬ አያሌው ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።