በላሊበላ ነዋሪዎች ከጦርነት ለማገገም እየታገሉ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበውና ከትግራይ ክልል ድምበር በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው ላሊበላ ከተማ ከጦርነቱ በፊት የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ ነበር። በጦርነቱ ምክንያት ግን የተለያዩ አስተዳዳሪዎች በተፈራረቁባት ከተማ ከአለት ተፈልፍለው የተሰሩትን ቤተክርስቲያናት ለማየት ይደረግ የነበረውጉብኝት አሁን ቆሟል።

ሄነሪ ዊልኪንስ ከዚህ ሁኔታ ለማገገም የሚደረገውን ጥረት ቃኝቶ ከላሊበላ ያደረሰንን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።