ኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጆችን መታሰር እና የጅምላ መቃብርን ውንጀላ ውድቅ አደረገች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት በትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማጽዳትና የጅምላ እስር በምዕራብ ትግራይ ይፈጸም ነበር የሚሉ ክሶችን የያዙ ሪፖርቶች ታይተው ነበር። የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅቶች እና ጋዜጠኞች ወደዚሁ አካባቢ እንዳይገቡ ባለሥልጣናት ሲከለክሉ ቆይተዋል። የአሜሪካ ድምፅ ወደዚሁ ምዕራብ ትግራይ ለሌሎች ያልተፈቀደ ግን በቁጥጥር የተሞላ ጉብኝት ለማድረግ ዕድል አግኝቷል። ለእስርና የጅምላ መቃብር ውለዋል የተባሉትንም ቦታዎች ለማየት ችሏል።