የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ምሬት

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፈው ሳምንት ቀዳሚ ርእስ ሆኖ የሰነበተው በአዲስ አበባ ከተማ ነጋዴዎች ላይ የተደረገው አዲሱ አማካኝ የቀን ገቢ ትመና አሁንም ነጋዴዎችንና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን አላግባባም። ገቢዎች የገቢ ግምት ትመናው የቀን ገቢን እንጂ ተከፋይ ግብርን አያሳይም ሲል የነጋዴው ማኅበረሰብ አባላት በበኩላቸው ግምቱ ወደፊት ሊመጣ የሚችለውን ከፍተኛ የገቢ ግብር ማሳያ በመኾኑ ሊቀበሉት እንደማይችሉ ይናገራሉ። ተከታዩ የጽዮን ግርማ ዘገባ ይህንን ሁኔታ ያስቃኘናል።