በሶማሊያ ላይ የተጣለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጠየቁ

Your browser doesn’t support HTML5

ላለፉት 30 ዓመታት በሶማሊያ ላይ ተጥሎ የቆየው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንዲነሳ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር በመሆን ጥሪ አቀረበች

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ ሞሀሙድ በኢትዮጵያ ባደረጉትን የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማጠቃለያ ላይ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሰጡት የጋራ መግለጫ፣ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ማዕቀቡ እንዲነሳ በሶማሊያ መንግሥት የቀረበውን ጥሪ እንዲቀበል ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡

ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት የሚያደርጉትን ጋራ ጥረጥ ሊያደናቅፉ የሚችሉ ያሏቸውን ያልተገቡ የውጭ ጣልቃ ገብ ተጽዕኖዎችን መቀነስ እንደሚገባና ሽብርተኝነትን በተሳካ ሁኔታ መዋጋት እንደሚገባ አፅንዖት መስጠታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡