ያልተቋጨው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና ውዝግቦቹ

Your browser doesn’t support HTML5

በመቀሌ የሚካሔዱ የድሮን ጥቃቶች መቀጠላቸውን የህወህት ባለሥልጣናት እየገለጹ ነው።

የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ባለፈው ቅዳሜ በመቀሌ በሚገኙ የሲቪል መኖሪያ አካባቢዎች ጥቃት ተፈጽሟል ሲሉ የፌዴራል መንግሥቱን ከሰዋል ፡፡

በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በበኩላቸው “ህወሓት የመንግሥት ድሮኖች በሲቪል ተቋማት ላይ እያነጣጠሩ ነው የሚል ድራማ እያሰራጨ ነው” ብለዋል።

በሌላ ተያያዥ ዜና፣ ኤርትራ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለማሳተፍ ለተጠባባቂ ወታደሮቿ ጥሪ እያቀረበች መሆኗን የብሪታንያ እና የካናዳ መንግሥታት እንዳሳወቁ ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በበኩላቸው ተጠባባቂዎችን ከመጥራት ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ የሚሰራጩ መረጃዎችን የሀሰት ዜና ስለመሆናቸው ገልጸዋል፡፡

ኤርትራ በሰሜን ኢትዮጵያ አሉታዊ ሚና እየተጫወተች ስለመሆኗ በአውሮፓ ሕብረት የቀረበባትን ክስም አስተባብላለች፡፡

እንደገና ያገረሸው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እልባት ሳያገኝ ቀጥሏል።