የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና የሚሰሙት ሰላም ጥረቶች

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሃመር በፌዴራል ኃይሎች እና በትግራይ አማፂያን መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ 12 ቀናት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ አቅንተዋል፡፡

ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት ለሰላም ድርድር ያለውን ተስፋ ያጨለመ ሲሆን፣ የኤርትራ ሃይሎችም ተመልሰው ወደ ጦርነቱ ገብተዋል መባሉን ጨምሮ እና በሱዳን ድንበር አካባቢ ውጊያ መጀመሩን ተከትሎ ግጭቱ እንዳይስፋፋ ሥጋት ፈጥሯል፡፡

በሌላ በኩል 35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስቸኳይ በሚል ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ ቆመው የእርቅ ንግግሮች እንዲጀመሩ” ጠይቀዋል፡፡