የኢትዮጵያ ሕግጋት በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል ቋት ተዘጋጀ

  • እስክንድር ፍሬው

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ

የኢትዮጵያን ሕግጋት ማንም ተጠቃሚና የሚፈልግ ሰው በቀላሉ እንዲያገኛቸው ለማድረግ የታሰበ የመረጃ ቋት ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያን ሕግጋት ማንም ተጠቃሚና የሚፈልግ ሰው በቀላሉ እንዲያገኛቸው ለማድረግ የታሰበ የመረጃ ቋት ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

ይህ የመረጃ ቋት ከ1934 ዓ.ም. እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ የወጡ ሕግጋትንና ደንቦችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲን አሠራርም “ለተገልጋዮች ቀላል ቅርበት እንዲኖረው የሚያደርግ” የተባለ የኢንተርኔት አገልግሎትም ይፋ ተደርጓል።

እንደዚህ ዓይነት አሠራሮች “በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት በተግባር ያግዛሉ” ሲሉ ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ብርሃኑ ፀጋዬ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ ሕግጋት በቀላሉ ለማግኘት የሚያስችል ቋት ተዘጋጀ