ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በሱዳን
Your browser doesn’t support HTML5
ዛሬ ካርቱም የገቡት የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ሸንጎ መሪ ሌተናል ጄኔራል አብዱልፋታህ አልቡራህን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በካርቱም ለውጥ ከመጣበት ከሁለት ወራት በፊት አንስቶ ኢትዮጵያና ሱዳን እየተመካከሩ ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከአሥር ቀናት በፊት ከአሜሪካን ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረው ነበር፡፡ የዛሬ ጉዟቸውም የዚያ ምክክር ሂደት አካል በዚያ ቃለ መጠይቅ ያስረዱት፡፡