አዲስ አበባ —
ኤችአይቪ ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር ፓትሪሽያ ሃስላክ ገለፁ፡፡
ምናልባትም ሃገሪቱ ከኤድስ ነፃ ትውልድ በመፍጠር ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለኤድስ አጣዳፊ ድጋፍ መርኃግብር - ፔፕፋር አሥረኛ ዓመትም አዲስ አበባ ላይ በአሜሪካ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከብሯል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያን መንግሥት ወክለው የተገኙት የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ፈይሣ የተገኘው ውጤት ሊቀለበስ እንደማይችል ተናግረዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5