አዲሱ የኢትዮጵያ ፓርላማ ሰኞ ስራ ይጀምራል

  • እስክንድር ፍሬው

የኢትዮጵያ ፓርላማ

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ መቶ በመቶ የሚቆጣጠረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሪዎቹን ይመርጣል

የፊታችን ሰኞ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዲስ እንደራሴዎች ስራ የጀምራሉ። ሁለቱም የህግ አውጭ አካላት በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ መቶ በመቶ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ናቸው።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ኢህአዴግና አጋር ድርጅቶቹ 547ቱን መቀመጫዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ

የስራ ዘመኑን የፈጸመው ፓርላማ

ሰኞለት የሚሰየመው ፓርላማ የጠቅላይ ሚኒስትር ምርጫ የሚያከናውን ሲሆን፤ ገዥው ፓርቲ የሚመሰርተውን መንግስት ማለት የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ተከትሎ ይቀርባል።

የኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክርበትና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀዳሚነት አፈ ጉባዔዎቻቸውን እንደሚመርጡ የወጣው የጊዜ ሰሌዳ ያስረዳል።

Your browser doesn’t support HTML5

የድምጽ ዘገባ ከአዲስ አበባ (በእስክንድር ፍሬው)