ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋራ ይጀመራል የተባለው ድርድር ተስፋ እንደፈነጠቀላቸው ነዋሪዎች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ነገ በታንዛኒያ ይጀመራል የተባለው ድርድር የሰላም ተስፋ እንደፈነጠቀላቸው ሁለቱ አካላት በሚዋጉባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ገለጹ።

ግጭት ካለባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት ነዋሪዎች፣ ድርድሩ ለዓመታት የዘለቀውን አለመረጋጋት ሊያስወግድ ይችላል በሚል ተስፋ መደሰታቸውንም ተናግረዋል፡፡ ሁለቱም አካላት ሕዝቡን ተሳቢ በማድረግ በቅንነት እንዲደራደሩም ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድ በሁለቱ ወገኖች መካከል ነገ ድርድር እንደሚጀመር ትላንት ይፋ ያደረጉ ሲሆንየኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም የሠላም ውይይቱ በሦስተኛ ወገን አደራዳሪነት እንደሚካሄድ አረጋግጧል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።