የኦሮሞ ተማሪዎች ጥያቄ ከጀርባው “የቀለም አብዮት” አራማጆች እጅ አለበት ሲሉ አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባ —
ባለፉት ሣምንታት በኦሮሚያ የተለያዩ ክፍሎች ተቀስቅሶ በነበረው የተማሪዎች ተቃውሞና የተከተለው ሁከት ምክንያት “ከታሠሩት አንዳንዶቹ የተፈቱ ቢሆንም ዛሬም እሥሩ ቀጥሏል” ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ዋና ፀሐፊና የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ገልፀዋል፡፡
አቶ በቀለ ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ለነገ በስተያ ቅዳሜ የጠራው ሰልፍም ዓላማው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግሥትን የግድያና የእሥራት እርምጃ በአንድነት የሚቃወምበት መድረክ መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ባለስልጣናት የኦሮሞ ተማሪዎች ተቃውሞ ሕጋዊ መሆኑን ጠቅሰው ከእንቅስቃሴው በስተጀርባ ግን “የቀለም አብዮት” ያሉትን የሚያራምዱ ሊኖሩ እንደሚችሉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ገልፀዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገበ ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5