የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጥ አስገዳጅ እንጂ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለውም - ባለሞያዎች

Your browser doesn’t support HTML5

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ ለኢትዮጵያ የ3ነጥብ4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ማጽደቁን አስታውቋል፡፡

“የተራዘመ የብድር አቅርቦት”(ECF) በተባለው ፕሮግራም ከጸደቀው ብድር ውስጥ፣ አንድ ቢሊዮን ዶላር በአፋጣኝ ለኢትዮጵያ የሚለቀቅ እንደኾነ ተቋሙ ገልጿል።

ይህም ኢትዮጵያ፣ የውጭ ምንዛሬ ግብይቱ በገበያ እንዲወሰን የፖሊሲ ለውጥ ማድረጓን ባስታወቀች ማግስት ይፋ የኾነ ነው፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የፋይናንስ እና ምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች፣ ብድሩ፥ በውሳኔው ምክንያት የሚመጣውን ኢኮኖሚያዊ መናጋት ለማስተካከል እንዲያግዝ ታስቦ የተፈቀደ ሊኾን ይችላል፤ ይላሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔም በአይኤምኤፍ አስገዳጅነት የተወሰነ እንጂ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለውም፤ ሲሉ ይገልጻሉ፡፡