የኢቦላ ስብሰባ በአዲስ አበባ

  • እስክንድር ፍሬው

የአፍሪካ ኅብረትና ኢቦላ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢቦላ ስብሰባ በአዲስ አበባ

ባለፈው ሣምንት ውስጥ የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ትብብር ተቋሙ ኢጋድ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሮችና ባለሙያዎች አዲስ አበባ ላይ ተሰብስበው ኢቦላ ተከስቶ በነበረባቸው አካባቢዎችና ዓመታት የነበረውን ልምድ መነሻ በማድረግ ሊደረግ በሚገባው ጥንቃቄና ዝግጅት ላይ ተነጋግረዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ጥናታዊ ፅሁፎችን ካቀረቡት ባለሙያዎች መካከል የሕክምናና የኅብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያው፣ በኢትዮጵያና በሌሎችም የአፍሪካ ሃገሮች የበሽታዎች ሥርጭትና ቁጥጥር ላይ የሠሩት ዶ/ር አያና የኔአባት ይገኙበታል፡፡

እስክንድር ፍሬው አነጋግሯቸዋል፤ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡