ግንቦት ሃያ ከግራና ከቀኝ

  • መለስካቸው አምሃ

ግንቦት ሃያ



ግንቦት ሃያ

Your browser doesn’t support HTML5

ግንቦት ሃያ ከግራና ከቀኝ


ኢህአዴግ ሥልጣን የያዘበትን ሃያ ሦሶተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ዛሬ ባሰሙት ንግግር “በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እየተገነባ ነው” ብለዋል።

የገዥው ፓርቲ ኢሕአዲግ አንዳንድ አመራር አባላት ለዴሞክራሲ እንቅፋት እንደሚፈጥሩ ገልፀው ይህ ችግር “በተለመደው የድርጅቱ አሠራር ይወገዳል” ብለዋል፡፡

“የዴሞክራሲውን ግንባታ ወደኋላ ጎትተውታል፤ ለአሸባሪዎች እና ለአክራሪ የገበያ ኃይሎች ይላላካሉ” ያሏችውን የፖለቲካ ድርጅቶች እንቅስቃሴም በህግ እንመክታለን ብለዋል።

የአንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ግን “በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እየተገነባ አይደለም፥ ከአሸባሪነት ጋር ግንኙነት ያለው ፓርቲም የለም” በማለት ያስተባብላሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ።