በነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ ወቅቱን ያገናዘበ አለመሆኑን አንድ ባለሞያ ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ መንግሥት የነዳጅ ውጤቶች መሸጫ ላይ ካለፈው ሚያዚያ 30 ጀምሮ የዋጋ ጭማሪ አድርጓል። ጭማሪውን ተከትሎም ክልሎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ እያደረጉ ናቸው። ዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በነዳጅ ማረጋጊያ ድጎማው ላይ ወደ 10 ቢሊዮን ብር ጉድለት በማስመዝገቡ ጭማሪውን ለማድረግ መገደዱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሞያዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፕሮፌሰር መንግሥቱ ከተማ ግን “ውሳኔ ወቅቱን የጠበቀ አይደለም” ይላሉ። በነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው ጭማሪ የዋጋ ንረቱን ሊያባብሰው እንደሚችልም ሥጋት አላቸው።