"ኤርትራዊያን ከኢትዮጵያዊያን ጋር በፍቅር ሊኖሩ ጓጉተዋል"- ዘጋቢያችን ብርሃነ በርኸ ከአስመራ
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ በአስመራ ታሪካዊ በተባለ ጉብኝት ተገናኝተው የሁለትዮሽ ምክክር ጀምረዋል። እሁድ ማለዳ በአስመራ አየር ማረፊያ የሁለቱ ሀገሮች መሪዎች ሲጨባበጡና ሲተቃቀፉ፤ በሽዎች የተቆጠሩ የአስመራ ነዋሪዎችም በመንገድ ዳር ተኮልኩለው ሲጨፍሩ ታይቷል። አስመራ በኢትዮጵያና ኤርትራ ባንዲራ ደምቃ ታይታለች።