አሳዛኙ የስደት እልቂት

Your browser doesn’t support HTML5

ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ከ170 በላይ የሚሆኑ ስደተኞችን ከአቅሙ በላይ የጫነ ጀልባ ቅዳሜ ለሊት በሚዲትራኒያን ባህር ሰምጦ አራት ስደተኞች ብቻ ሲተርፉ ሌሎቹ ህይወታቸውን ማጣታቸውን አንድ የስደተኞች መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ከተረፉት ስደተኞች ሁለቱ ኤርትራዊ ሁለቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ አንዷ እርጉዝ ሴት እንደሆነች አጀንሲያ አበሻ የተባለው ስደተኞችን የሚረዳው ቡድን መሪ አባ ሙሴ ዘርዓይ፤ የጣሊያን ባህር ሃይልን ጠቅሰው ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።