"የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ስደተኞችን በተመለከተ ምን እያደረጉ ነው?" አባ ሙሴ ዘርዓይ

Your browser doesn’t support HTML5

በዚህ ዓመት ብቻ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች ወደ ደቡባዊ የአውሮፓ ሀገራት ለመድረስ የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጠዋል። ጣልያንና ማልታ በየባህር ወደቦቻቸው የደረሱ ስደተኞችን አንቀበልም በማለታቸው ምክንያት በርካታ ስደተኞች ሜዲትራኒያን ባህር ላይ ህይወታቸውን እያጡ ነው። ሜዲትራኒያንን ባቋረጡ በርካታ ስደተኞች በሚጠሩዋቸው ቅፅል ስም "የስደተኛ አባት" አባ ሙሴ ዘርዓይ አጀንሲያ ሀበሻ የተሰኘ የምግባረ ሰናይ ድርጅት መስራችና ስራ አስኪያጅ ናቸው።