አወዛጋቢው የምርጫ 2007 አጠቃላይ ይፋ ውጤት እና የተቃዋሚዎች ምላሽ

  • እስክንድር ፍሬው
    መለስካቸው አምሃ
    ሔኖክ ሰማእግዜር

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሊቀ-መንበር ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በግንቦርት ወረ ታካሂዶ የነበረውን ምርጫ ይፋ ውጤት አስታወቁ።

Your browser doesn’t support HTML5

አወዛጋቢው የምርጫ 2007 አጠቃላይ ይፋ ውጤት እና የተቃዋሚዎች ምላሽ


ኢሕአዴግና አጋሮቹ የግንቦት 16ቱን ምርጫ 100 በመቶ ለማሸነፍና 547ቱንም የፓርላማ መቀመጫዎች ሙሉ በሙሉ ለመያዝ የአንድ የምርጫ ክልል ውጤት ብቻ ይጠብቃሉ።

የምርጫውን አጠቃላይ ውጤት ዛሬ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፥ ኢሕአዴግና አጋሮቹ ከ547 የፓርላማ መቀመጫዎች፥ 546ቱን ማሸነፋቸውን አመልክቷል። ውጤቱ እየተጠበቀ ያለው ብቸኛው የግል ፓርላማ አባል ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የተወዳደሩበት የቦንጋ ጊምቢ ቦጎአካ የምርጫ ክልል ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ “የምርጫው ውጤት ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጭኜ መግዛት እችላለሁ የሚለውን መልእክት ኢሕአዴግ ያስተላለፈበት ነው፤” ሲሉ አንድ የመድረክ አመራር አባል ተናገሩ። የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዘዳንት በኩላቸው ውጤቱ አላስገረመኝም ብለዋል።

እስካሁን ይፋ በሆኑ የምርጫ ውጤቶች ያልተገለጸው አንድ መቀመጫ የግሉ ተወዳዳሪ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የተወዳደሩበት ቦንጋ ጊምቦ ጎአታ የምርጫ ክልል ጨምሮ በእለቱ አቢይ ርዕስ የተዳሰሱትን ዘገባዎች ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ።