ለውጭ ባለሀብቶች እየተከፈተ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ - በጫና ወይስ በዕቅድ?

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ አድርጋቸው የነበሩ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ቀስ በቀስ እየከፈተች ትገኛለች፡፡

መንግሥት ከዓመት በፊት፣ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጉን አስታውቋል፡፡ አሁን ደግሞ፣ በኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ብቻ ተይዘው የነበሩ የሸቀጥ ምርቶችን የመሸጥ እና የማከፋፈል የንግድ ሥራዎችን ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት ለማድረግ እየተዘጋጀ መኾኑን ገልጿል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የኢኮኖሚ ባለሞያዎች፣ መንግሥት የሚያደርጋቸው ዐዲስ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ በዓለም ባንክ ጫና የመጡ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡

“ኢኮኖሚው እንዲህ ዐይነት ለውጦች ያስፈልጉታል፤” ያሉት ባለሞያዎቹ፣ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችም ከወዲሁ አብሮ በሽርክና ለመሥራትና ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፤ ብለዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።