በድሬደዋ ከተማ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለሙስሊም ምዕመናን ያዘጋጁት አፍጥር

Your browser doesn’t support HTML5

በድሬዳዋ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ወጣቶች ከራሳቸውና ከከተማዋ የንግድ ማኅበረሰብ ገንዘብ በማስባሰብ ለሙስሊም ምዕመናን በከተማዋ “ለገሐሬ” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የመንገድ ላይ አፍጥር መርሐ ግብር አዘጋጅተው ነበር። ምዕመናኑ የከተማዋ ክርስትያን ወጣቶች ባዘጋጁት የአፍጥር መርሃ ግብር ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን እነሱም በክርስትያን በዓላት ላይ ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።