መምህር ምህረተ አብና ፌቨን ዘሪሁንን ጨምሮ 12 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

Your browser doesn’t support HTML5

ከኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተፈጠረው ችግር ጋራ በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉት መምህር ምህረተ አብና ፌቨን ዘሪሁንን ጨምሮ 12 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ፖሊስ እነዚህን ግለሰቦች “ሕገ መንግሥት እና ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ፣ ኅብረተሰቡን ለሽብር በማነሳሳት ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ” ሲል ለችሎት ማስረዳቱን ከተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች አንዱ ዲያቆን ዘካሪያስ ወዳጅ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

በተጠርጣሪ ጠበቆች በኩልም ክርክር መደረጉን የገለጹት ጠበቃና የሕግ አማካሪው፣ ችሎቱ ከተጠርጣሪዎች መካከል አምስቱ ላይ ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሲፈቅድ የተቀሩት በዋስ እንዲፈቱ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡

ባልደራስ ፓርቲም ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ ከቤተክርስቲያኗ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አባሎቼ እየታሰሩና እየተሳደዱ ነው ብሏል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም፣ መንግሥት በሁከት ተግባር ላይ የተሠማሩትን በቁጥጥር ሥር አውዬ ለሕግ ማቅረቤን እቀጥላለሁ” ማለቱ ይታወሳል፡፡

በቤተክርስቲያኗ የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንግሥት ጋር በተለያዩ ነጥቦች ላይ መስማማታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ከችግሩ ጋር በተያያዘ በመደበኛ መንገድ አገልግሎት እንዳይሰጡ የታገዱ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን አሁንም እንደተዘጉ ናቸው፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።