አዲስ አበባ —
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ተከስሰው እሥር ቤት ውስጥ በሚገኙ ሦስት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት ላይ ዛሬ ተጨማሪ የእሥራት ቅጣት ወስኗል፡፡
በነዘላለም ወርቅአገኘሁ ዶሴ ከተከሰሱት መካከል የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበሩት ዳንኤል ሺበሺ፤ የአረና ትግራይ አመራር አባል የነበሩት አብረሃ ደስታና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል የነበሩት የሺዋስ አሰፋ ችሎት በመድፈርና በማንጓጠጥ ከዋናው ክሥ ውጭ ነው የተወነጀሉት፡፡
አቃቤ ሕግ በሰባተኛው ተከሣሽ ላይ ያሻሻለውን ክሥ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎታል፡፡
ተከሣሾቹ በተያዘው ቀጠሮ የእምነት ክሕደት ቃል ይሰጣሉ ተብሏል፡፡