ኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን እንዳያስገቡ አገደች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎችን እንዳያስገቡ እግድ ተጣለ፡፡

እነዚኽ አካላት በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እንዲያስገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፈላቸው ደብዳቤ አሳስቧል፡፡

ርምጃው፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ አካል እንደኾነ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ ተናግረዋል፡፡