ጋቢና ቪኦኤ የወጣቶች ፕሮግራም አንድ አመት አስቆጠረ
Your browser doesn’t support HTML5
በጋቢና ቪኦኤ ፕሮግራማችን ባሳለፍነው አንድ አመት ውስጥ ወጣቶችን የሚመለከቱ የተለያዩ ነጥቦችን በማንሳት ባለሙያዎችን ወደ ስቱዲዮ ጋብዘን ነበር። ጤና ፣ ስደት፣ ኢትዮጵያዊነት፣ የአየር ንብረትን በተመለከተ ትኩረት በመስጠት፤ በተለያዩ ሙያዎች ላይ የሚገኙ ወጣቶችን ከኢትዮጵያ፣ ከአውሮፓ፣ ከተለያዩ አረብ ሃገራትና ከዩናይትድ ስቴትስ የህይወት ተሞክሯቸውን አካፍለውን ነበር። ለትውስታ ዛሬ የተወሰኑትን እናሰማችኃለን። ለሙሉ ዘገባው ከበታች ያለውን ተንቀሳቃሽ ምስል ይጫኑ።