ውዝግብ ባስነሳው ፈተናዎች ውጤት ላይ ትምሕርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጠ

Your browser doesn’t support HTML5

ውዝግብ ባስነሳው ያለፈው ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ውጤቶች ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ መደረሱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ግን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር አለመነጋገሩን ቅሬታና ሥጋታቸውን በይፋ ካሳወቁት መካከል የሚገኘው የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም አመልክቷል። አሁንም ጥያቄዎች እንዳሉ ዋና እምባ ጠባቂው ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ተናግረዋል። የፈተና ሥርቆት ዋነኛ ችግር መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለእንደራሴዎቹ ገልፀዋል።