የእነአቶ አንዱዓለም ይግባኝ ውድቅ ተደረገ

አቶ አንዱ ዓለም አራጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ




Your browser doesn’t support HTML5

የእነአቶ አንዱዓለም ይግባኝ ውድቅ ተደረገ


በአሸባሪነትና በአገር ክህደት ወንጀል ተከስሰው በተፈረደባቸው በአቶ አንዱ ዓለም አራጌ፣ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በአቶ ናትናኤል መኮንንና በሌሎችም ላይ የበታች ፍርድ ቤት ቀደም ሲል ያሣለፈውን ፍርድ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አፀና።

የእነ አቶ አንዱዓለም አራጌ ጠበቆች ደምበኞቻቸው ከፈቀዱ ጉዳዮን ወደ ሰበር ችሎት ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ።

በምኅፃር ሲፒጄ የሚባለው የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋች ዓለምአቀፍ ድርጅት - Committee to Protect Journalists የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባሣለፈው ውሣኔ ላይ፣ በተለይ ስለ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባወጣው መግለጫ “… ፖለቲካዊ ፍርድ ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ያላትን ገጽታ ያዋርዳል …” ብሏል። “ፍርዱ በጣም አሳሳቢ የሆነው በአሸባሪነት ወንጀል ላይ የሚቀልድ በመሆኑ ነው” ብሏል ድርጅቱ በመግለጫው አክሎ።

የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ድርጅት - ሲፒጄ


ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አባል እንደመሆኗ ዓለምአቀፍ ሕግንና የራሷንም ሕገመንግሥት በማክበር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እስክንድርን ከእሥር ቤት መፍታት እንደሚገባትም ጠቅሷል።

ሲፒጄ በመግለጫው “እስክንድርና ሌሎች ጋዜጠኞችን ማሰቃየት የሚያስተዳድረውን ሕዝብ ሃሣብ የሚፈራ መንግሥት ምልክት ነው” ብሏል።

የፍርዱን ሂደት የተከታተለው ዘጋቢአችን መለስካቸው አምሃ ዘገባ ተያይዟል፤ ያዳምጡት።