ኤርትራ ውስጥ “በማዕድን ልማት ላይ የግዳጅ ሥራ ይሠማራል፤ በሃገሪቱ ውስጥ የከፋ አፈና አለ” ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ባለፈው ሣምንት ያወጣውን ክስ ኤርትራ አስተባብላለች፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
ለሂዩማን ራይትስ ዋች የግዳጅ ሥራ ክሥ የኤርትራ መንግሥት ምላሽ
Your browser doesn’t support HTML5
ሂዩማን ራይትስ ዋች በኤርትራ የግዳጅ ሥራ ስለመኖሩ በሠነዘረው ክሥ ላይ ከአምባሣደር ግርማ አስመሮም ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ
Your browser doesn’t support HTML5
የሂዩማን ራይትስ ዋች ክሥ ሪፖርት - “ኤርትራ የግዳጅ ሥራ ትጠቀማለች”
ቢሻ የወርቅ ማዕድን ሥፍራ - ኤርትራ
ኤርትራ ውስጥ “በማዕድን ልማት ላይ የግዳጅ ሥራ ይሠማራል፤ በሃገሪቱ ውስጥ የከፋ አፈና አለ” ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ባለፈው ሣምንት ያወጣውን ክስ ኤርትራ አስተባብላለች፡፡
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሂዩማን ራይትስ ዋችን “ስም በማጥፋት የፀና” ሲል ከስሶታል፡፡
አምባሣደር ግርማ አስመሮም - በአፍሪካ ሕብረትና በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ አምባሣደር
በአፍሪካ ሕብረትና በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኤርትራ ውስጥ “የግዳጅ ሥራ የለም” ብለዋል፡፡
ቢሻ የወርቅ ማዕድን ሥፍራ
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣውና ትናንት በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ ዌብሣይት ላይ በሠፈረው “ሂዩማን ራይትስ ዋች፡- በቋሚ የስም ማጥፋት ተልዕኮ ላይ” ሲል በሰየመው መግለጫው “የድርጅቱ መሠረተ-ቢስ ክሦች በኤርትራ ሃገራዊ አገልግሎት እና እያቆጠቆጠ ባለው የማዕድን ልማት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው” ብሏል፡፡
መግለጫው አክሎም ሂዩማን ራይትስ ዋች ኤርትራን በራሱ አስተያየት የሰብዓዊ መብቶች ረጋጭ ሃገር እንደሆነች የገለፀበትን ሃገራዊ አገልግሎቷን ከግዳጅ ሥራ ጋር ሃፍረት በሌለው ሁኔታ አተካከክሎታል - ብሏል፡፡
ድርጅቱ ወደዚህ ድምዳሜ የደረሰው ማንም እራሱን የሚያከብር ተመራማሪ ወይም አጥኚ ከቁብ ሊቆጥረው በማይችል የምርመራ ዘዴ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዋች ኤርትራን “የሰብዓዊ መብቶች ረጋጭ ነች” ያለው በሰገን እና በቢሻ ከተቀጠሩት በጥቅሉ 1330 ሠራተኞች አራቱን ብቻ አነጋግሮ መሆኑን የኤርትራ መንግሥት መግለጫ ጠቁሞ እነዚህ የተጠያቂዎችን የአንድ ከመቶ አንድ ሦስት ሺህኛ አስተያየት መሠረት ያደረጉ ድምዳሜዎች ከቁም ነገር መውሰድ የሌለባቸው በቁጥሩ እጅግ አነስተኛ መሆን ምክንያት ብቻ ሣይሆን ሂዩማን ራትስ ዋች የሰዎቹን ቃላት እንዳሉ ወይም በግርድፍ አወራረዳቸው በመውሰዱም ጭምር ነው” ብሏል፡፡
“ሂዩማን ራይትስ ዋች የተበላሸ ሪፖርቱን ለማስረገጥ ያጠቀሰባቸው ሌሎቹ ዋነኛ የጀርባ ምንጮቹ አንድም በሃገሪቱ ላይ የጥላቻ አጀንዳ ያላቸው አንዳንድ መንግሥታት፣ ወይም/እና ክብር የለሽ ከሃዲዎች ናቸው” ብሏል፡፡
ዝርዝሮቹን ከተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ