የኤርትራ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሌ መሪዎች - በአስመራ
Your browser doesn’t support HTML5
የኤርትራው መሪ ፕረዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌው ፕረዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ዛሬ ጥር 18 አስመራ በሚገኘው ቤተ-መንግሥት ተገናኝተው የሦስትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። መሪዎቹ በአገራቱ መካከል የተጀመረውን ግንኙነት እና አስቀድመው የተደረሱ ስምምነቶች የደረሱበትን ደረጃ በተመለከተ እንዲሁም ለሦስቱም ሃገራት አስፈላጊነት ባሏቸው የቀጠናውና አህጉራዊ ጉዳዮች ከተወያዩ በኋላ የጋር መግለጫ አውጥተዋል።