ኢሕአዴግና አብዮታዊ ዴሞክራሲው

  • ቪኦኤ ዜና
ኢሕአዴግ

ኢሕአዴግ

አቶ ሬድዋን ሁሴን - የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ

አቶ ሬድዋን ሁሴን - የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ

Your browser doesn’t support HTML5

ኢሕአዴግና አብዮታዊ ዴሞክራሲው

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ኢትዮጵያን “ልማታዊ ዴሞክራሲ የምታራመድ ሃገር” ፖሊሲዎቹንም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሲል ይገልፃል።

ተቃዋሚዎቹ ደግሞ “ምን የሚሉት ፖሊሲ ነው? ዲሞክራሲም ልማትም የላትም” በማለት ይሟገታሉ።

ላለፉት ሃያ አራት ዓመታት ሥልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ፖሊሲዎቹ አብዮታዊ ዲሞክራሲ እና ልማታዊ ዴሞክራሲ እንደሆኑ ይናገራል።

በነዚህ ፖሊሲዎች ቀደም ባሉ ዓመታት በከባድ ረሃብ ትመታ የነበረችው ሃገር አሥር ከመቶና ከዚያ በላይ ወይም ባለሁለት አኀዝ የምጣኔ ሃብት ዕድገት ማስመዝገቧ ይነገርላታል፡፡

መንግሥታቸው "አብዮታዊ ዴሞክራሲ" የሚለውን የመንግሥቱ ቃል አቀባይ አቶ ሬድዋን ሁሴን ሲያብራሩ “ዴሞክራሲን በዘገምተኛ መንገድ ቀስ በቀስ መገንባትን መምረጥ ይቻላል፤ ወይም በአብዮታዊ፣ በሥር-ነቀል እርምጃ ሥርዓቱን እንዳለ መቀየር፤ ሌላው አማራጭ ነው። አስተሳሰቡን እንዳለ ከሥረ-*መሠረቱ ጀምሮ ቅርንጫፎቹን ሁሉ ባፋጣኝና ሙሉ በሙሉ መቀየር - አብዮታዊ ማለት ይሄ ነው” ብለዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ እና የመድረክ ምልክቶች

የሰማያዊ ፓርቲ እና የመድረክ ምልክቶች

ይሁን እንጂ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲን የመሳሰሉት ትላልቆቹ ፓርቲዎች “ልማታዊ ዲሞክራሲ” የሚባለውን ይነቅፋሉ፡፡ አባሎቻችን በፖሊስና በገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች እያስፈራሩና እያዋከቡ ባሉበት ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ይሆናል የተባለውንም እንደማይቀበሉ ሲናገር ቆይተዋል፡፡

በየነ ጴጥሮስ - ፕሮፌሰር /የመድረክ ሊቀመንበር/

በየነ ጴጥሮስ - ፕሮፌሰር /የመድረክ ሊቀመንበር/

የመድረክ ሊቀመንበር ዶክተር በየነ ጴጥሮስ ሰማንያ በመቶ ህዝቧ በገጠር በሚኖርባት ሃገር የዕድገቱ ፍሬ ወደ ብዙኃኑ አልወረደም ይላሉ።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡