ኢትዮጵያ ውስጥ ለኮሮናቫይረስ መጋለጡ የተረጋገጠ ሰው የለም

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ ውስጥ እስከ አሁን ለኮሮናቫይረስ መጋለጡ የተረጋገጠ ሰው የለም። የመከላከልና የክትትል ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በኢንስቲትዩቱ ከዚህ ቀደም ተመርምረው ከቫይረሱ ነጻ ከሆኑት ናሙናዎች ውስጥ 45 በመቶው ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልከው ዳግም መመርመራቸው እና ውጤቱ ተመሳሳይ መሆኑ መረጋገጡንም ጨምሮ አመልክቷል።