የምርጫውን ውጤት አንቀበልም - በደቡብ አንድ የመድረክ ተጠሪ

  • ሔኖክ ሰማእግዜር

Medrek Election Observer in Bulgita Shone

ክሡ መሠረተ-ቢስ ነው - በደቡብ አንድ የምርጫ ፅ/ቤት አስተባባሪ

ደቡብ ኢትዮጵያ፣ በምሥራቅ ባዳቾ ወረዳ የስቄ ቁጥር 2 ምርጫ ጣቢያ ድምፅ ቆጠራ ሲካሄድ - ዕሁድ፤ ግንቦት 16/2007 ዓ.ም

Your browser doesn’t support HTML5

የምርጫ ውዝግብ በደቡብ ኢትዮጵያ

ከሰባ ሁለቱ የምሥራቅ ባዳቾ የምርጫ ጣቢያዎች በሃያ ሁለቱ ላይ ታዛቢዎቻችን ተባረሩ ሲሉ በደቡብ ክልል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የምሥራቅ ባዳቾ ወረዳ ሊቀመንበር ክሥ አሰሙ፡፡

አቶ ኤልያስ አደሮ - የመድረክ የምሥራቅ ባዳቾ ወረዳ ሊቀመንበር

ሊቀመንበሩ አቶ ኤልያስ አደሮ በትናንቱ ድምፅ አሰጣጥ ወቅት “በአምስት ቀበሌዎች ውስጥ ባሉ ጣቢያዎች ላይ የመድረክ ታዛቢዎች ሳይደርሱ ኮሮጆዎች ተከፍተው ተሞልተው አድረዋል” ብለዋል፡፡

የመድረክ የወረዳው ሊቀመንበር አክለውም “በየደረጃው ያሉ የገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት፣ ታጣቂዎችና ካድሬዎች በየምርጫ ጣቢያው እየተዘዋወሩ ሰዉን ሲያስፈራሩና ማንን መምረጥ እንዳለበት ሲናገሩና ሲያስገድዱ ነበር” ሲሉ ከስሰዋል፡፡

“ውጤቱ የአፈና ምርጫ ውጤት ነው - ያሉት አቶ ኤልያስ - ውጤቱን አንቀበልም፤ ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን፤ ለዓለም ማኅበረሰብ እናሳውቃለን፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እናሳውቃለን፤ ወደኋላ አንልም፤ ቆዝመን ወደቤት አንገባም” ብለዋል፡፡

አቶ ያዕቆብ ዮሴፍ - የምሥራቅ ባዳቾ ወረዳ የስቄ 02 ምርጫ ክልል አስተባባሪ

በሌላ በኩል ግን የምሥራቅ ባዳቾ ወረዳ የስቄ 02 ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ያዕቆብ ዮሴፍ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ “ሕዝቡ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በንቃት ሲሣተፍ ውሏል፣ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ተካሂዷል፤ ሕዝቱ የምርጫ ሕጉን በተከተለ መልኩ ድምፁን ሲሰጥ ውሏል” ብለዋል፡፡

የመድረክ የምሥራቅ ባዳቾ ወረዳ ሊቀመንበር አቶ ኤልያስ አደሮ ያሰሙትን ክሥ አስመልክቶ ክሥ በቀረበባቸውና ሄደው ባይዋቸው ጣቢያዎች የመድረክ ታዛቢዎች ጨርሶውኑ አለመከሰታቸውን ገልፀው “ክሡ ተጨባጭነት የለውም” ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡