በምስራቅ ወለጋና በሆሮ ጉድሩ የእርስ በእርስ ግጭት ከመቀስቀሱ በፊት መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ኢሰመኮ ጠየቀ

  • መለስካቸው አምሃ

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮምያ ክልል በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ወደ ማኅበረሰብ ግጭት እንዳያመሩ ያለውን ሥጋት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን አስታወቀ።

ግጭቶጭ በሚደጋገሙባቸው አካባቢዎች መንግሥት በቂ የጸጥታ አስከባሪዎችን እንዲልክ ሲልም አሳሰበ።