የግብጽ አየር መንገድ አውሮፕላን አስገድዶ ቆጵሮስ እንዲያርፍ ያደረገው ጠላፊ በቁጥጥር ስር ውሏል
Your browser doesn’t support HTML5
የግብጽ አየር መንገድ አውሮፕላን አስገድዶ ቆጵሮስ እንዲያርፍ ያደረገው ጠላፊ በቁጥጥር ስር መዋሉንና መንገደኞቹ ታግተው የቆይበት ሁኔታም ማብቃቱን የደሴቲቱ ሀገር ባለልሥጣናት ገለጡ። የቆጵሮስ መንግሥት ቃል አቀባይ ኒኮስ ክሪስቶዱሊደስ በትዊተር ባወጡት መግለጫ ዛሬ ማክሰኞ ላርናካ አውሮፕላን ጣቢያ ተገዶ ያረፈው አውሮፕላን መንግደኞችና የበረራ ሰራተኞች በደህና ሁኔታ ላይ ናቸው ብለዋል።