የትምሕርት ጉዳይ:- ለምን እንማራለን?

ዶ/ር አያሌው ገብረ ሥላሴ

“የኢትዮጵያ ሕዝብ (በተራ ሕዝብነት የምንመለከተው) ብዙ ዕውቀትና አስተዋይነት ያለው ነው። ከእነሱ ብዙ ተምሬያለሁ። ደግሞም ስለነሱም ነው ከበሬታ ያለኝ። በኢትዮጵያዊነት፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር፥ እንግዳ ተቀባይነት ለሌላው ማሰብ፥ ሲታመም ሄዶ መጠየቅ፤ ይሄ ይሄንን ሳይ ይነካኛል።”ዶ/ር አያሌው ገብረስላሴ የትምሕርት ባለሞያ።

በትምሕርት (ምርምርና ጥናት) የአንድ ሰው የዕድሜ ልክ ጉዞ።

በመምሕርነትና በትምሕርት ሥራ አመራር የሥራ መስኮች በቀድሞው የኢትዮጵያ የትምሕርት ሚንስቴር ሠርተዋል። ኋላም በተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምሕርት ጉዳዮች አማካሪነት ለረዥም ዓመታት አገልግለዋል።

ዛሬ ደግሞ በጡረታ ዘመናቸው፤ ላለፉት በርካታ ዓመታት የለት-ተቀን ሥራቸው ባደረጉት የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች የሥርዓተ-ትሕርት ቀረጻ ተጠምደው ይገኛሉ። ዶ/ር አያሌው ገብረስላሴ ይባላሉ።

ቆይታ ከዶ/ር አያሌው ገብረ ሥላሴ ጋር

​ላለፉት በርካታ ዓመታት መኖሪያቸው ባደረጓት የምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትሷ የአሌግዛንደሪያ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ጎራ ብለን ሥራቸውን፤ ለትምሕርት ብልጽግና እና ለነገው ሰው ቀና መንገዶች የታለመ ረዥም ጉዟቸውን ቃኘት አድርገናል። በአጫጭር ተከታታይ ክፍሎች የቀረቡትን የቃለ ምልልሱን የመጀመሪያ ሦሥት ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በትምሕርት፥ ምርምርና ጥናት የአንድ ሰው የዕድሜ ልክ ጉዞ .. ክፍል አንድ

Your browser doesn’t support HTML5

ትምሕርትና ሠው የመሆን ነገር .. ክፍል ሁለት

Your browser doesn’t support HTML5

በወላጅና በመምሕራን እና በወላጅና በልጅ መካከል ያሉ ግንኙነቶች ምንነት .. ክፍል ሦሥት