በዓለም ዙሪያ ከ150 ሚሊየን በላይ ህፃናት ለአዕምሮ ጤና ችግር ተዳርገዋል - ዩኒሴፍ

Your browser doesn’t support HTML5

በዓለም ዙሪያ ከአንድ መቶ ሃምሳ ሚሊየን በላይ ህፃናት ለአዕምሮ ጤና ችግር መዳረጋቸውን የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት አጣዳፊ ድጋፍ ፈንድ /ዩኒሴፍ/ አስታውቋል።
ችግሩ አፋጣኝ መፍትኄ ካልተበጅለት ለህይወት አስጊ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችል ዩኒሴፍ አዲስ ባወጣው የዓለም ህፃናት ሁኔታ ሪፖርት ላይ አስጠንቅቋል።
የህፃናቱን የአዕምሮ ጤና ሁኔታ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያሳደራቸው ጫናዎች እያባባሱት መሆኑንም ሪፖርቱ ይናገራል።