በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ በተነሳ ግጭት አስር ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ሲዳማ ክልል አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

- የኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ፀጥታ ኃላፊ የሞቱ ሁለት ናቸው ብለዋል

በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ ላይ በሚገኙ ጉቦሄማ እና ቦጨሣ በተባሉ አከባቢዎች በተከሰተ ግጭት የሰላማዊ ሰዎች ቤቶች መቃጠላቸውንና በሺሆች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች አስታወቁ።

የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በግጭቱ አስር ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ከሁለቱም በኩል በግጭቱ እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ 92 ግለሰቦች መታሰራቸውን ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ፀጥታ ኃላፊ አቶ መሐመድ ኪሶ በበኩላቸው መጠነኛ ያሉት ግጭት እንደነበረ ገልፀው የሚያውቁት ሁለት ሰው ብቻ መገደሉን እንደሆነ ጠቁመዋል። ጉዳዩ በሽምግልና መያዙን እና የተፈናቀሉትም ወደቤታቸው እየተመለሱ መሆናቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።