ኮሮናቫይረስ ከተከሰተ በኋላ ከ3መቶ ሃምሳ በላይ ህፃናት ተድረዋል

Your browser doesn’t support HTML5

በአማራ ክልል በዘንድሮው ዓመት በተለይ የኮሮናቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ ከ3መቶ ሃምሳ በላይ ህፃናት ያለ ዕድሜያቸው እንዲዳሩ መደረጉን የክልሉ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ። ለጋብቻው መጨመር የት/ቤቶች መዘጋት ምክንያት መሆኑን ቢሮው አክሎ ገልጿል። የክልሉ ፖሊስ በበኩሉ ቁጥሩ የተጋነነ ነው ብሏል።