ትረምፕ በሰማኅታት መቃብር ላይ ፎቶ መነሳታቸው ነቀፌታን አስከትሏል

Your browser doesn’t support HTML5

የቀድሞው ፕሬዝደንትና የሪፐብሊካን ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ እጩ ዶናልድ ትረምፕ፣ አርሊንግተን በሚገኘው የሰማኅታት መቃብር ላይ ፎቶ መነሳታቸው ነቀፌታን ያስከተለ ሲሆን፣ አንዳንድ የሰማኅታቱ ቤተሰቦች ግን ድጋፋቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው። የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ እጩ ካመላ ሄሪስም ድርጊቱን “ፖለቲካዊ ትኩረት ለማግኘት” የተደረገ ነው ሲሉ አውግዘዋል።

ቬሮኒካ ባልዴራስ ኢግሌሲያስ የላከችው ዘገባ ነው።