መጭው 100 ቀናት ለዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ “የሞት ሽረት” ይሆናሉ ተባለ

Your browser doesn’t support HTML5

የሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንታዊ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ እና የዴሞክራቲክ ፕሬዝደንታዊ ዕጩ ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስ፣ አንድ ጊዜ የሪፐብሊካኑን እጩ ሌላ ጊዜ ደግሞ የዲሞክራቱን ዕጩ በመምረጥ በሚታወቁት ግዛቶች ለማን ድምጻቸውን እንደሚሰጡ እስካሁን ያልወሰኑ መራጮችን ቀልብ ለመግዛት ጥረት በያዙበት በአሁኑ ወቅት፤ አንዱ በሌላው ላይ የተነጣጠረ የሰላ ጥቃት መሰንዘራቸውን ቀጥለዋል።

ሁለቱ ወገኖች ከሦስት ወራት አነስ ያለ ጊዜ ብቻ ለቀረው ምርጫ በየፊናቸው በሚያካሂዱት የምረጡኝ ዘመቻ ፉክክርም ‘ይበልጥ ተጋግሞ ይቀጥላል’ ተብሎ ተጠብቋል። የአሜሪካ ድምጿ ቬሮኒካ ባልደራስ ኢግሌሲያስ ያደረሰችንን ዘገባ ዝርዝር ይዟል፡፡