ድርቅ እና የሰብዓዊ ድጋፍ በኢትዮጵያ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የምግብ እርዳታ ፈላጊ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ማደጉን የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጿል።

በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ወደ 16 ሚሊዮን የሚጠጋ ቁጥር ያለው ሕዝብ የምግብ እርዳታ ፈላጊ መሆኑን ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል።

የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ሰሞኑን ድርቅ ከተከሰተባቸው አካባቢዎች አንዱ ወደሆነው ቦረና ዞን ተጉዞ ያናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።