“ከብቶቻችን በድርቁ መሞት ጀምረዋል” የቦረና ነዋሪዎች

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ በአምስት የተለያዩ ክልሎች ከደረሰው ድርቅ የቦረና ዞኑ የከፋ በመሆኑ ከብቶች መሞት መጀመራቸውን ነዋሪዎች ገለጹ። በጥቂት ቀናት ውስጥ ዝናብ መጣል ካልጀመረ ደግሞ ለከፋ አደጋ እንደሚጋለጡ በመግልጽ አሁን ያለውን የግጦሽ መሬት መድረቅ በ1977 ዓ.ም ከደረሰው አስከፊ ድርቅ ጋር ያያይዙታል።