የድሮን አጠቃቀምን በተመለከተ ወጥ ሕግ እንዲኖር የመስራት ዕቅድ አለኝ
Your browser doesn’t support HTML5
ሊዲያ ረዘነ በአፍሪካ ማላዊ የአፍሪካን ቴክኖሎጂ ማዕከል የአነስተኛ ሰው አልባ በራሪ መሳሪያዎች(ድሮን)ምህንድስና እየተማረች ተገኛለች፡፡ ከሁለት ወራት በኃላ ወደ ኢትዮጵያ ሰትመለስ የድሮን አጠቃቀምን በተመለከተ ወጥ ሕግ እንዲኖር የመስራት ዕቅድ አላት፡፡ በቆጵሮስ እና በቻይና የበረራ እና የሕዋ ምህንድስና ተምራለች፡፡ የኢትዮጵያ ሳተላይት ETRSS-1 ላይ ተሳታፊ ነበረች፡፡ አሁን ላለችበት ደረጃ ቤተሰቦችዋን በተለይም አባትዋ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ትናገራለች፡፡