ቡና ጠጡና “ዕድሜ ጥገቡ” - ጥናት

Your browser doesn’t support HTML5

አንዲት ስኒ ቡና! አቦል ካለበለዚያም እስከ በረካው - የብዙ ሰው ሱስና የለት ተለት ቀጠሮው ነው። በተለይ በጠዋት “ፉት” የተባለች እንደሁ አህ!!! መልካም ቀን ተጀመረ ማለት ነው… አንድ ሰሞኑን የወጣ አዲስ የጥናት ሪፖርት ደግሞ “ምን ቀን ብቻ? ዕድሜ ሙሉ እንጂ!” ይላል። በቀን ሦስት ስኒ ቡና የሚያጣጥሙ ሰዎች ከማይጠጡቱ ለተሻለ የዘመን ርዝማኔ እንዲሁ እንዳጣጣሙት ይኖራሉ፡፡