“የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል” ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

  • እስክንድር ፍሬው

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

በተለያዩ ክልሎች ላለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ እና ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ ካልተሰጠ አገሪቱ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ልታመራ እንደምትችል የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስጋታቸውን ገልጹ።

የሰልፈኞችን ጥያቄዎች ማድመጥና ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ማክበር ይህ እንዳይሆን እንቅፋት የሆኑ አዋጆችን መሰረዝ ቀዳሚው እርምጃ ሊሆን እንደሚገባም ዶ/ር ነጋሶ ጠቁመዋል።

በኦሮምያና አማራ ክልል እየተካሄዱ ያሉት ተቃውሞዎች እንደሚያሳሱቧቸው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ገልጸዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

“የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ወደ እርስ በእርስ ግጭት ሊያመራ ይችላል” ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ